Habesha2day
Welcome
Login

Technology and Science


 • ቫይበር በስህተት የላክነውን መልእክት ከላክንለት ሰው ስልክ ላይ እንድናጠፋ አስቻለ

   

  አንዳንድ ጊዜ ሳናስበው ወይም በድንገት የተሳሳተ መልእክት ለሰው ልከን እንዴት አድርጌ ያ ሰው መልእክቱን ሳያየው ወይም ሳያነበው ላጥፋው የሚለው ጥያቄ ሲፈጠርብን ይስተዋላል።የጽሁፍ፣ የድምጽ እና የምስል መልእክት ለመላላክ በስፋት የምንጠቀምበት ቫይበር ግን ለዚህ መፍትሄ ነው ያለውን አዲስ የአገልግሎት ማሻሻያ ማቅረቡን አስታውቋል።

  በቫይበር አዲሱ የአገልግሎት ማሻሻያ መሰረትም የአንድሮይድ እና አይ ኦ ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚጠቀሙ ስማርት ስልኮች ላይ በስህተት የላክነውን መልእክት ከራሳችን ስልክ ላይ ብቻ ሳይሆን ከላክንለት ሰው ስልክ ላይም ማጥፋት እንችላለን።ይህ አገልግሎት አንድ ለአንድ ወይም በህብረት /ግሩፕ/  በሚደረግ የመልእክት ልውውጦች ላይ እንደሚሰራም ቫይበር አስታውቋል።

  ነገር ግን ወደ እኛ የተላከውን መልእክት ስናጠፋ ራሳችን ጋር ብቻ ያለውን እንጂ የላኪው ጋር ያለውን ማጥፋት እንደማንችል ተነግሯል።በአዲሱ የቫይበር ማሻሻያ ላይ በስልካችን ላይ ያለ ፋይልን ለሌሎች ማስተላለፍ ወይም ማያያዝ /አታች/ ለማድረግ የሚያስችል ትግበራም ተካቶበታል።ከአንድ ፋይል በላይ የምንልክ ከሆነም እያንዳንዱን ፋይል ለየብቻ የሚልክ መሆኑም ተገልጿል።እስክ 200 ሜጋ ባይት የሆነ ማንኛውን ፋይል በአንድ ጊዜ መላክ እንደሚቻልም አስታውቋል።

  ምንጭ፦ timesofindia. com/tech

   

   

  Read more »
 • ኮርዶን ብሉ የሚባሉ ወፎች ለጓደኞቻቸው ሲዘምሩ እንደሚደንሱ ሳይንቲስቶች አስታወቁ፡፡

   

  ጃፓንና ጀርመን ሳይንቲስቶች ፈጣን እንቅስቃሴን በሚያሳይ ካሜራ ወፎቹ ሲደንሱ ለመመልከት ችለዋል፡፡

  በጣም አስገራሚ ነው ያሉት የጥናቱ ተባባሪ ማንፍሬድ ጋህር ስላልታየ እንጂ ተመሳሳይ ዳንስ በሌሎች የወፍ ዝርያዎችም ሊደነስ ይችላል ብለዋል፡፡ጥናቱ በ16 ካርዶን ብሉ ወፎች ላይ የተካሄደ ሲሆን ወፎቹ በአብዛኛው ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት የሚገኙ ናቸው፡፡አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ወፍ በማድረግ ለሁለት ሰዓታት አብረው አንዲቆዩ በማድረግ ነው የወፎቹን የዳንስ ችሎታ ለማየት የቻሉት፡፡

  የወፎቹ አስገራሚው ነገር የሚደንሱት ለሚወዱት ጓደኛቸው ብቻ መሆኑ ነው ሲሉ የሆካይዶ ዩንቨርሲቲው ተመራማሪ ማሳዮ ሶማ ተናግረዋል፡፡ወፎቹ የሚያደርጉትን ዳንስ በዓይን መመልከት እንደማይችል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

  Read more »
 • ራስፕ ቤሪ አዲሱንና በጣም ርካሽ የተባለውን የትምህርት መርጃ ኮምፒውተር ለገበያ አቀረበ።

  አዲሱ ኮምፒውተር በ5 የአሜሪካ ዶላር እንደሚሸጥም ነው የተገለፀው።የኮምፒውተር ግኝቱ በጣም አነስተኛና በኪስ የሚያዝ ሲሆን፥ በተለይም ህፃናትን ለማስተማር ተመራጭ መሆኑም ተነግሯል።“ራስፕቤሪ ፒ ዚሮ” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ኮምፒውተር፥ መቀመጫውን እንግሊዝ ባደረገው ድርጅት የተሰራ ነው።ግኝቱ የመጨረሻ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ማሻሻያዎች የተተገበሩለትና በኮምፒውተር እገዛ መማር ለሚሹ ጠቃሚ መሆኑም ተጠቅሷል።

  cheap.jpg

  ኮምፒውተሩ ባለ1 ጊጋ ኸርዝ ኤ አር ኤም ፕሮሰሰር፣ 512 ሜጋ ባይት ራም እና ማይክሮ ኤስ ዲ ካርድ የሚቀበል፣ አነስተኛ የኤች ዲ ኤም አይ ሶኬት ያለውና የዩ ኤስ ቢ ኬብል የሚቀበል ነው።በዚህ ዓመት ቢቢሲ ከራስፕ ቤሪ ፒ እና ከሌሎችም የኤሌክትሮኒክስ አምራች ተቋማት ጋር በመቀናጀት  “ዘ ማይክሮቢት” የተሰኘውን የራሱን የልጆች ማስተማሪያ ኮምፒውተር ይፋ ማድረጉም ይታወሳል።

  ኮምፒውተሩ በመላው ዩናይትድ ኪንግደም ኮዲንግ የተሰኘውን ትምህርት ለማስተማር ዕድሜያቸው ከ11 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት በነፃ ተከፋፍሏል።የኮዲንግ ትምህርት በእንግሊዝ በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ፖሊሲ  ውስጥ ተካቶ እየተሰጠ ይገኛል።

  ምንጭ፦ www.cnet.com

   

  Read more »
 • አዲሱ "ላይ ፋይ" ገመድ አልባ ኔትዎርክ

  አሁን አሁን ገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎት ዋይ ፋይ /Wi-Fi/ በርካታ ስፍራዎች አገልግሎት ላይ ሲውል እናስተውላለን።የዋይ ፋይ ኔትዎርክ ባለበት ስፍራም ስልካችንንም ይሆን ሌሎች የኤሌክትሮኒስ መገልገያ ቁሶቻችንን በቀላሉ  በማገናኘት ያለ ተጨማሪ ገመድ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎትን መጠቀም ያስችለናል።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን የቴክኖሎጂው ዘርፍ ተመራማሪዎች ከዋይ ፋይ በጣም የተሻለ ገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎት አግኝተናል እያሉ ነው።

  በተለያየ ጊዜ በተደረገ ሙከራም ላይ ፋይ ከዋይ ፋይ በእጥፍ የፈጠነ ነው ሲሉም ተናግረዋል።ላይ ፋይ በሴኮንድ የአንድ ጊጋ ባይት ፍጥነት ያለው መሆኑን የሚናገሩት ተመራማሪዎቹ፥ ይህም ጥራት ያላቸውን /HD/ ፊልሞች በሴኮንዶች ውስጥ ማውረድ ያስቻል ሲሉ በማሳያነት አስቀምጠዋል።በአሁኑ ጊዜም ቴክኖሎጂውን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ በቢሮዎችና በኢንዱስትሪ በተስፋፋባቸው ስፍራዎች ሙከራ እየተደረገበት መሆኑም ተነግሯል።

  ላይ ፋይ ኔትዎርክ መረጃን ለማሰራጨት ብርሃንን ይጠቀማል የተባለ ሲሆን፥ በጥቅም ላይ ያለመብራት በቀላሉ በኔትዎርክ አማካኝነት መረጃን እንዲያስተላልፉ ያደርጋል።የላይ ፋይ ቴክኖሎጂ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011 የኤዲንበርግ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር በሆኑት ሃራልድ ሃስ ነው የተሰራው።በወቅቱም የፈጠራው ባለቤት የሆኑት ፕሮፌሰር ሃራልድ ሃስ ቴድ ላይ ተገኝተው የሰጡት ማብራሪያ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ እና በዩትዩብ ገጽ ላይ ብቻ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ተመልካቾችን ያገኘ ነበር።

  ከዋይ ፋይ በተሻለ ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ እና በፍጥነት መረጃን ለማስተላለፍ ይረዳል የተባለለት ላይ ፋይ /Li-Fi/ በአሁኑ ጊዜ በአየር መንገዶች እና በተለያዩ የደህንነት ተቋማት እየተሞከረ መሆኑ ተነግሯል።

  ምንጭ፦ www.telegraph.co.uk

   

  Read more »
 • በፀሃይ ሀይል የሚሰራው የመጀመሪያ አውቶብስ ሙከራውን በተሳካ መልኩ አጠናቋል

   በፀሃይ ሀይል የሚሰራው የመጀመሪያው አውቶብስ ሙሉ በሙሉ ሙከራውን በተሳካ መልኩ አጠናቋል።በቲቤት ላህሳ ከተማ ውስጥ ሙከራ የተደረገባቸው 27 አውቶብሶች በአሁኑ ጊዜ መንገደኞችን ማጓጓዝ መጀመራቸው ተነግሯል።በፀሃይ ሀይል የሚሰሩት አውቶብሶቹ ከዚህ በፊት በኤሌክትሪክ ከሚሰሩት አውቶብሶች ጋር ተመሳሳይ ሲሆኑ፥ ልዩነቱ ጣራው ላይ ነው ተብሏል።

  ይህም የአውቶብሱ ጣራ ላይ የፀሀይ ሀይል ለመሰብሰብ የሚረዳው የሶላር ፓኔል የተገጠመለት በመሆኑ ነው።አውቶብሱ በተገጠመለት ፓኔል አማካኝነት የሚያገኘውን ሀይል ተጠቅሞ ነው የሚንቀሳቀሰው።

  አውቶብሱ ቀኑን ሙሉ በሚያገኘው የፀሃይ ሀይል አማካኝነት የሚንቀሳቀስ ሲሆን፥ የፀሀይ ሀይል በሚያንስበት ጊዜም በተገጠመለት ባትሪ አማካኝነት ነው የሚንቀሳቀሰው።

  በነዳጅ ሀይል ከሚሰራው አውቶብስ ጋር ሲነጻጸር የመሸጫ ዋጋው ትንሽ ይወደዳል የተባለው  አውቶብሱ፥ በቀጣይ አገልግሎት በሚሰጥበት ጊዜ ግን ወጪ ቆጣቢ በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል ተብሏል።

  ሙሉ በሙሉ በፀሃይ ሀይል ከተሞላም በእንድ ጊዜ እስከ 260 ኪሎሜትር መጓዝ እንደሚችል ተነግሯል።ከሁሉም በላይ ግን አውቶብሶቹ የዓየር ብክለትን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ መሆኑ ነው የተጠቆመው ።

  ምንጭ፦ en.people.cn

  Read more »
RSS