Habesha2day
Welcome
Login

News and Events


 • የዓለም ባንክ አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጡ ምክንያት ለደረሰባት ችግር የሚሆን የ16 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ስራ ዕቅድ ይፋ አወጣ

   

   

  በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት አፍሪካ ላይ እየደረሰ ያለው ችግር ከባድ እንደሆነና አነስተኛ የሰብል ምርት፣ የምግብ ዋጋ መጨመር እንዲሁም ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ የጤና እክሎች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያንን እስከ 2030 እ.ኤ.አ ወደ ከፋ ድህነት እንዳይጨምሩ ተሰግቶአል።

  የዓለም ባንክ መፍትሔ ይሆናል ብሎ ያቀደውን የንግድ ሥራ ያስታወቀ ሲሆን እቅዱም የአየር ንብረት ለውጡ ካስከተለው ችግር በፍጥነት ለማገገምና ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያለው ልማት ለማምጣት እንደሚጠቅም ተገልጿል። ይህም እቅድ የአህጉራቱ የተፈጥሮ፣ የቁሳዊ፣ የሰውና ማህበራዊ ሀብቷን በአግባቡ እንድትጠቀምና የአየር ለውጡ ካስከተለው ለውጥ ጋር በሚጣጣም ሁኔታ በፍጥነት ካጋጠማት ችግር ማገገም እንድትችል የሚያግዝ ነውም ተብሏል።

   

   

  Read more »
 • Turkey to hand over Russia pilot's body

   

  Turkey says it has received the body of a Russian pilot killed after his plane was shot down on the Syrian border.The body of Lt Col Oleg Peshkov will be given back to Russia, Prime Minister Ahmet Davutoglu said.Turkish forces shot down the plane saying it had violated Turkish airspace, which Russia denies.

  The incident has led to heated rhetoric between the two countries, with Russia announcing a package of economic sanctions against Turkey.Mr Davutoglu said that Lt Col Peshkov's body had been treated in accordance with Orthodox Christian tradition.Another pilot in the plane, Capt Konstantin Murakhtin, survived and was rescued from rebel-held territory in Syria in a special forces operation.Capt Murakhtin said he wanted to go back to duty and stay in Syria, saying "someone has to pay" for his colleague's death.

  A decree signed by President Vladimir Putin on Saturday covers imports from Turkey, the work of Turkish companies in Russia and any Turkish nationals working for Russian companies.The decree also calls for an end to charter flights between the countries.Turkish President Recep Tayyip Erdogan has refused to apologise to Russia over the incident.

  On Friday, he accused Moscow of "playing with fire" in its Syria operations. But on Saturday, he said he was "saddened" by the downing of the jet.Turkey and Russia have important economic links. Russia is Turkey's second-largest trading partner, while more than three million Russian tourists visited Turkey last year.

  source bbc

  Read more »
 • ድንበር ተሻጋሪ ሰብዕና

  "መለስ በህዝቦቹ ጥቅም የማይደራደር ነበር "                             

                                 ፖል ካጋሜ

  "የአፍሪካ እውነተኛ ልጅ ፣ ለሀገሪቱ ያበረከተው አስተዋፅኦ ከቃላት በላይ ነው  "                  

                                  ታቦ ምቤኪ                                                   

  "የምርጥ አዕምሮ ባለቤት ፤ የኩሩ ህዝብ ኩሩ መሪ "                                                

                                   ሱዛን አልዛቤት ራይስ

  "ሁሌም የሀገሩንና የአፍሪካን ችግር አስመልክቶ የሚሰጠውን ትንታኔ መስማት ያስደስተኛል "                             

                                      ባን-ኪ-ሙን

  "የበርካታ ችግረኞችን እጣ ፈንታ ለማቃናትና ድህነትን ለመቀነስ የተጋ መሪ"

                                       ባራክ ኦባማ

  Read more »
 • ፌስቡክ የተጠቃሚዎችህን መረጃ ስጠን የሚሉኝ መንግስታት በዝተዋል አለ

   

  አሜሪካ በ3 ወር ውስጥ ከ26 ሺህ 500 በላይ ተጠቃሚዎቼን መረጃ ጠይቃኛለች

   ታዋቂው የማህበራዊ ድረገጽ ፌስቡክ፣ የተጠቃሚዎቹን የግል መረጃዎች አሳልፎ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁት መንግስታት ቁጥር እያደገ መሆኑን ማስታወቁን ሲኤንቢ ኒውስ ዘገበ፡፡

  መሰል መረጃዎችን አሳልፎ እንዲሰጣቸው ከመንግስታት የሚቀርቡለት ጥያቄዎች ቁጥር በ2015 የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በ18 በመቶ ማደጉን የገለጸው ፌስቡክ፣ ባለፉት የጥር፣ የካቲትና መጋቢት ወራት ብቻ ከተለያዩ የአለም አገራት መንግስታት 41 ሺህ 214 ጥያቄ እንደቀረበለት አስታውቋል፡፡ 

  የተጠቃሚዎቹን የግል መረጃ እንዲሰጡት ከጠየቁት መንግስታት መካከል የአሜሪካ መንግስት ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዝ የጠቆመው ፌስቡክ፣ የአሜሪካ መንግስት በሶስቱ ወራት ከ26ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን መረጃ አሳልፌ እንድሰጠው 17 ሺህ 577 ጥያቄዎችን አቅርቦልኛል ሲል ገልጧል፡፡
  በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ህንድ 5 ሺህ 115፣ እንግሊዝ 3 ሺህ 384፣ ፈረንሳይ 2 ሺህ 520፣ ጀርመን 2 ሺህ 344 መሰል ጥያቄዎችን እንዳቀረቡለት ያስታወቀው ፌስቡክ፣ የምመራበት ፖሊሲ የተጠቃሚዎቼን የግል መረጃ አሳልፌ እንድሰጥ ስለማይፈቅድልኝ ጥያቄያቸውን አላስተናገድኩም ብሏል፡፡

  Read more »
 • ፍቅረኛን ለማስደመም እስከህይወት መስዋዕትነት!?

  ቻይናዊው ሁ ሴንግ አንዲት የሚወዳት ፍቅረኛ አለችው፡ እናም ፍቅሩን ለመግለፅ ብቻ ሳይሆን Surprise ሊያደርጋት (ሊያስደምማት) ያስብና ትንሽ ይቆዝማል - ሃሳብ እያወጣ እያወረደ፡ ብዙዎቹ የመጡለትን ሃሳቦች አናንቆ ጣላቸው - ፍቅረኛውን ለማስደመም ብቃት እንደሌላቸው በመቁጠር፡፡ በአዕምሮው የሃሳብ ጅምናስቲክ ሲሰራ ቆይቶ ግን አንዲት ሃሳብ አንጀቱ ላይ ጠብ አለችለት፡፡ ሃሳቡን ለመተግበርም ሲበዛ ተጣደፈ፡፡ ፍቅረኛውን ሊያስደምምበት በወጠነው ሃሳብ እሱ ራሱ ቀድሞ ተደመመና ቁጭ አለ፡፡ ከድማሜው ሲወጣ ሃሳቡን ወደ ተግባር ለውጦ የማሰቡን በረከት ሊቋደስ ቋመጠ፡፡ በቻይና የቾንኪዊንግ ግዛት ነዋሪ የሆነው ሴንግ፤ ፍቅረኛውን በምን ሰርፕራይዝ እንደሚያደርጋት ለማንም አልተናገረም፡፡ ምስጢር ነው - እሱና እሱ ብቻ የሚያውቁት፡፡ ፍቅረኛውም የምታውቀው ሰርፕራይዝ ከተደረገች በኋላ ይሆናል፡፡ ሁሴንግ በቀጥታ የሄደው እንደ ዲኤች ኤል ያለ ፈጣን መልዕክት አድራሽ ተቋም ጋ ነበር፡፡ እዚያም እንደደረሰ ስለሚያደርሱት እቃ ወይም መልዕክት ምንነት ሳይናገር በካርቶን የታሸገ ስጦታ እፍቅረኛው ቢሮ እንዲወስዱለት ብቻ ተነጋገረና ተስማማ፡፡ የአገልግሎት ክፍያውንም ሳያቅማማ ፈፀመ፡፡

  Read more »
RSS