Habesha2day
Welcome
Login

ETHIOPIA NEWS


 • ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ከአቡ ዳቢ ልዑል አልጋወራሽ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

  ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአቡ ዳቢ ልዑል አልጋወራሽ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በሁለትዮሽና በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ምክክር አካሄዱ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአገሪቱ ልዑል አልጋወራሽና ምክትል የጦር ኃይል አዛዥ ጋር ያደረጉት ውይይት በኢኮኖሚያዊና አካባቢያዊ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።ውይይታቸውም የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ባለኃብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ ላይ በስፋት በሚሰማሩበትና የንግድ ልውውጡም በሚጠናከርበት እንደሆነ ውይይቱን የተከታተሉት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ገልጸዋል።ሁለቱ አገራት ባላቸው የንግድ ትስስርና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸው ጠንካራ የሚባል እንደሆነም ተገልጿል።

  በዓለም ላይ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እያስመዘገቡ ካሉት አገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በኢኮኖሚው መስክ ለተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ባለኃብቶች የተመቸች አገር አድርጓታል።የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ባለኃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱም ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላትም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ለልዑሉ አስረድተዋል።

  ልዑል አልጋወራሽ መሃመድ ቢን ዛይድ በበኩላቸው የአገራቸው ባለኃብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ እንዲሰማሩ እንደምታበረታታ ተናግረዋል።ሁለቱም ወገኖች ቀጣናዊ ሠላምና መረጋጋት ይበልጥ ትብብር በሚደረግበት ዙሪያ ምክክር አካሂደዋል።

  ኢትዮጵያና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በቀጣናዊ በተለይም በሶማሊያ፣ በሱዳንና በየመን ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ተመሳሳይ አቋም እንዳላቸው ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ገልጸዋል።የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ኅብረት የተመሰረተበትን 44ኛ ብሄራዊ ቀንን በማክበር ላይ ትገኛለች።የእንግሊዝ ውል መጠናቀቅን ተከትሎ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ታኅሳስ 2 ቀን 1971 በስድስት ፌዴሬሽኖች ኅብረት ነው የተመሰረተው።

  አቡ ዳቢ፣ ዱባይ፣ ኡም አል ኩዋይን፣ ሻርጃህ፣ ፉጃራህና አጅማን በኅብረት የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስን ሲመሰርቱ ራስ አል ካይማህ ደግሞ ከዓመት በኋላ ኅብረቱን ተቀላቅላለች።ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ወደ አቡ ዳቢ የተጓዙት በልዑል አልጋወራሽ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በቀረበላቸው ግብዣ ሲሆን፥ የአቡ ዳቢ ቆይታቸውን እንዳጠናቀቁ በዓለም የአየር ንብረት ጉባዔ ለመሳተፍ ወደ ፓሪስ ያቀናሉ።

  source fanabc

  Read more »
 • የውጭ ሀገራት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን በሀገር ውስጥ ያለፈቃድ ሲያሰራጩ በተገኙ ላይ እርምጃ ተወሰደ.

   

  ክፍያ የሚፈጸምባቸውን የውጭ ሀገራት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በሀገር ውስጥ ያለፈቃድ ሲያሰራጩ በተገኙ ላይ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እርምጃ መውሰድ ጀመረ።በባለስልጣኑ ፈቃድ አግኝቶ ሀገር ውስጥ ክፍያ ተፈጽሞባቸው የሚሰራጩ የውጭ ሀገራት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን እንዲያስተላልፍ ፈቃድ የተሰጠው መልቲ ቾይዝ ኢትዮጵያ አልያም "ዲ ኤስ ቲ ቪ" የተሰኘ ተቋም ብቻ ነው።ይሁንና ለባለስልጣኑ በደረሰ ተደጋጋሚ ጥቆማ አማካኝነት በተደረገ አሰሳ ክፍያ የሚፈጸምባቸውን የውጭ ሀገራት ፕሮግራሞች በህገ ወጥ መልኩ የሚያስተላልፉ መኖራቸውን ባለስልጣኑ ደርሶበታል።በዋነኛነትም የእግር ኳስ ውድድሮችን ጨምሮ ሌሎች ፕሮግራሞችን በቤይን ስፖርት፣ አቡዳቢ ስፖርትና ሌሎችንም ያለፈቃድ ሲያሰራጩ የነበሩ አካላት መገኘታቸውን ነው የባለስልጣኑ  የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ወርቅነህ ጣፋ ለጣቢያችን የተናገሩት።

  እግር ኳስን ጨምሮ ሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮችና ፊልሞች እየተላለፉባቸው የሚገኙት ካርዶችና ዲኮደሮች ተገቢው ግብርና ታክስ ተከፍሎባቸውና ሀገር ውስጥ ፍቃድ አግኝተው የማይሰሩ በመሆናቸው በህጋዊ መንገድ ታክስና ግብር በከፈሉበት ላይ ተጽእኖን ከመፍጠር በላይ ሃገሪቱ ተገቢውን ገቢ እንዳታገኝ ያደርጋሉ።እንደባለስልጣኑ ገለጻ እንዚህ ህገወጦች በርካታ የሚባሉ ደንበኞችን መዝግበው በመያዛቸው ካርድ ሲቋረጥባቸው ተደዋውለው ክፍያ እየተቀበሉ ፕሮግራሞችን ያሰራጫሉ።በዚህም መነሻነት ባለስልጠኑ ከፖሊስ ጋር ባደረገው ዘመቻ ካርዶችና ሌሎች ዲኮደሮችን ደብቀው ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አቶ ወርቅነህ  ተናግረዋል።

  በተጨማሪም እነዚህ ፕሮግራሞች በምስራቅ አፍሪካ የተከለከሉና ለሌሎች የአረብ ሀገራት የተፈቀዱ በመሆናቸው ቢቋረጡ እንኳን ዋስትና የሚባል ነገር እንደሌላቸው ነው ባለስልጣኑ የተናገረው።ባለስልጣኑ ህገ-ወጦች ላይ የጀመረውን እርምጃ በቀጣይ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቆ፥ ህብረተሰቡም የእነዚህ ህገ ወጦች መጠቀሚያ እንዳይሆን መጠንቀቅ ይኖርበታል ብሏል።

  source fanabc

   

  Read more »
 • የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት አዋጅ በሁለት ሳምንት ውስጥ ፀድቆ ወደስራ ሊገባ ነው

  የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት አዋጅ በመጪዎቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ፀድቆ ወደስራ እንደሚገባ ተነገረ።

  በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ የህዝብ አስተያየት ማሰባሰቢያ መደረክ አካሂዷል።

  በምድረኩ ላይ በአዋጁ ቢካተቱ፣ ቢስተካከሉና ቢቀነሱ ያሏቸውን ሀሳቦች ከባለድርሻ አካላት እና በውይይቱ ከተሳተፉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተነስተዋል።

  አዲሱ አዋጅ ወደ ውጭ ሀገራት የሚሄዱ ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች መፍታት የሚያስችሉና ጥቅሞቻቸውን በአግባቡ ማስከበር የሚያስችል መሆኑን ነው በመድረኩ ላይ የተጠቀሰው።

  የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ሲካሄድ የቆየው የግብዓተ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሮች ተጠናቀዋል።

  በመሆኑም በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ የውጭ ሀገራት የስራ ስምሪት አዋጁ ለምከር ቤቱ ቀርቦ ይፀድቃል ብለዋል።

  የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ አዋጁ ራሱ የሚያሰራ በመሆኑ መመሪያ እና ደንቡን የማውጣቱ ስራ ጎን ለጎን እየተካሄደ አዋጁን በቀጥታ ስራ ላይ ለማዋል ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል::

  Read more »
 • ኢትዮጵያ በቅርቡ ትራንስፎርመር ለውጭ ገበያ ማቅረብ ትጀምራለች

   

  (Habesha2day.com)ሃገሪቱ ለትራንፎርመር ግዥ ታወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ በማስቀረት የሃገር ውስጥ ፍላጎትን መሸፈን መቻሉን የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ገለፀ።

  የጎረቤት ሃገራትን ከፍተኛ የምርት ፍላጎት በአጭር ጊዜ ወሰጥ በማሟላትም ለሃገሪቱ የውጭ ምንዛሬን አስገኛለሁ ነው ያለው ፋብሪካው።

  ከትራንስፎርመር ጥገናና መቀየር ጋር ተያይዞ የአሰራር ክፍተቶችን ለመፍታትም ተቋሙ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

  የፋብሪካው ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ገብረኪዳን ገብረየስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ፋብሪካው በአመት የተለያዩ አቅም ያላቸውን 10 ሺህ ትራንስፎርመሮችን የማምረት አቅም አለው።

  እነዚህ ትራንስፎርመሮች ከ15 ሺህ ቮልት እስከ 33 ሺህ ቮልት አቅም ያላቸው የዲስትሪቢውሽን፣ የፓውርና ስፔሻል ትራንስፎርመሮች ናቸው።

  የምርቱ  ተጠቃሚ ከሆኑት አንዱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ፥ በፈለኩት መጠንና ጊዜ ትራንስፎርመር ከፋብሪካው እያገኘሁ በመሆኑ አገልግሎቴን ለማሻሻል አግዞኛል ብሏል።

  የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የውጭ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ገብረእግዚያብሄር ታፈረ፥ ትራንስፎርመሩ እዚሁ ሀገር ወስጥ መመረቱ የፈለጉትን ምርት በፈለጉት መጠንና ጊዜ እንዲያገኙ እንደረዳቸው ነው የገለጹት።

  የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ባደረገው የዳሰሳ ጥናት የሃገሪቱ ወቅታዊ የትራንስፎርመር ፍላጎት ከ13 ሺህ አይበልጥም።

  በዚህም መሰረት ይህንን ፍላጎት ቢበዛ በአንድ አመት ተኩል ውስጥ ማሟላት እንደሚቻል የገለፁት የኢንዱሰትሪው ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ አሰፋ ዮሃንስ፥ በአጭር ጊዜ ወስጥ የውጭ ገበያው ይጀመራል ብለዋል።

  በፋብሪካው የሚመረቱ ምርቶችም አለም የሚጠቀምበትን መሳሪያ ተጠቅመው ጥራቱን የማረጋገጥ ስራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

  ተቋሙ ለዘመናት አገልግሎት የሰጡና ያረጁ የማሰራጫ መስመሮችና ትራንስፎርመሮችን ለመቀየርም ከ60 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ በመመደብና የወጭ መሃንዲሶችን ጭምር በመቅጠር በአዲስ አበባና በስምንት ዋና ዋና የክልል ከተሞች እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

  በቡራዩ ከተማ የሚገኘው ፋብሪካው ሁለት ዋነኛ የስራ ክፍሎች አሉት።

  አንዱ የትራንስፎርመሩ ዋነኛ አካል(ቦዲ) የሚሰራበት ሲሆን፥ ሌላኛው ደግሞ የኤሌክትሪክ ስራው የሚሰራበትና ጥራቱ ተፈትሾ የሚወጣበት ክፍል ነው።

  source FBC

  Read more »
 • Ethiopian Airlines to order 10 narrow-body planes, eyeing CSeries or E2-CEO

   የEthiopia arilies ምስል ውጤት

  [Habesha2day.com] Ethiopian Airlines, Africa's largest carrier, wants to buy 10 narrowbody planes and is considering Canada's Bombardier and Brazil's Embraer jets among others, as it plans to nearly double its fleet between now and 2025, chief executive Tewolde Gebremariam said Monday.

  Tewolde, speaking on the sidelines of a global aviation forum in Montreal, said that he is visiting Bombardier's Mirabel factory on Tuesday to review the 100-seater CS100.

  He said in an interview that he is visiting the 100-seater CS100 at Bombardier's Mirabel factory on Tuesday, but is also considering aircraft made by the company's rivals."I'm also looking at E2, the Russians, the Japanese, the Chinese," he said.

  Ethiopian Airlines also has 14 firm orders for A350 aircraft between now and 2025. The carrier is looking at ordering 10 more aircraft, and is weighing B777 and A350 planes.

  Ethiopian Airlines expects to grow from 77 aircraft and 7.4 million passengers this year to 22 million passengers and 150 aircraft by 2025, he said. (Reporting by Allison Lampert; Editing by Bernard Orr; editing by Bernard Orr)

  Source Reuters

   

  Read more »
RSS