Habesha2day
Welcome
Login

Sport & Festivals


 • 7 የኬንያ አትሌቶች በአበረታች መድሀኒት ምክንያት ታገዱ

   

  የሁለት ጊዜው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮኗ ኤምሊ ቼቤትን ጨምሮ 7 ኬንያውያን አትሌቶች አበረታች መድሀኒት በመጠቀማቸው የኬንያ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን አግዷቸዋል፡፡ኤምሊ ቼቤት ለ4 አመታት የታገደችው ዲሪቲክ ፍሮሲሚድ የሚባል አበረታች መድሀኒት መጠቀሟ ስለተረጋገጠ ነው፡፡

  Read more »
 • በሴካፋ ዋንጫ ዋልያዎቹ ሩብ ፍጻሜ ተቀላቀሉ

   በ2015ቱ 38ኛው የምስራቅ አና መካከለኛው የእግር ኳስ ውድድር(ሴካፋ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ሩብ ፍጻሜ መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።በምድብ አንድ አስተናጋጇ ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ አቻዋ ጋር በሀዋሳ ስታዲየም የተጫወተች ሲሆን፥ ውጤቱም 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።በጨዋታው ታንዛኒያ በ51ኛው ደቂቃ ጎል አስቆጥረው ጨዋታውን መምራት ችለው የነበረ ሲሆን፥ ሙሉ የጨዋታው ሰዓት ተጠናቆ የባከነ ሰዓት ላይ የታንዛኒያ ብሄራዊ ቡድን በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠረው ግብ ዋልያዎቹ አቻ በሆነ ውጤት ጨዋታውን አጠናቀው ሊወጡ ችለዋል።

  በዚህም መሰረት ዋልያዎቹ ከምድብ አንድ ታንዛኒያ እና ሩዋንዳን ተከትለው በ4 ነጥብ በሶሰተኝነት አጠናቀዋል።ዋልያዎቹ ምርጥ ሶስተኛ በመሆን ወደ ሩብ ፍጻሜ መቀላቀል መቻላቸውንም አረጋግጠዋል።በምድብ ሁለት ኡጋንዳ እና ብሩንዲ በሀዋሳ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያካሄዱ ሲሆን፥ ኡጋንዳ ጨዋታውን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።የ13 ጊዜያት የሴካፋ አሸናፊዋ ኡጋንዳ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች።

  ከምድብ ሶስት ደቡብ ሱዳን በመጀመሪያ ተሳትፎዋ ወደ ሩብ ፍጻሜ ስታልፍ፥ ማላዊም ደቡብ ሱዳንን ተከትላ  ማለፏን አረጋጣለች።በተያያዘ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል የተባለውና ከሩብ ፍፃሜው እስከ ፍፃሜው ያለው ጨዋታ በሀዋሳ ሊካሄድ እንደሚችል በስፋት እየተነገረ ነው።ለዚህም የሴካፋ አወዳዳሪ አካላት፣ የውድድሩ ስፖንሰር እና የቴሌቪዥን አስተላላፊው ዲ.ኤስ.ቲቪ እንዲሁም በሀዋሳ የሚገኙት ቡድኖች በከተማውና መስተንግዶው በመደሰታቸው እና ቀሪ ውድድሮች በሀዋሳ እንዲካሄድ ፍላጎት በማሳየታቸው ነው ተብሏል። 

   

  Read more »
 • አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የ2015 የዓለም ምርጥ አትሌት ተብላ ተሸለመች

   

  አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የ2015 የዓለም ምርጥ አትሌት ተብላ ተመርጣለች።

  በወንዶች ደግሞ አሜሪካዊው አትሌት አሽተን ኤተን አሸንፏል።

  ሁለቱ አትሌቶች ትናንት ሽልማታቸውን ወስደዋል።

  በፈረንጆቹ 2015 ድንቅ ጊዜ ያሳለፈችው አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በቤጂንግ 15ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1 ሺህ 500 ሜትር የሩጫ ውድድር ማሸነፏ የሚታወስ ነው።

  በሻምፒዮናው በ5 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያኑ አትሌት አልማዝ አያና እና ሰንበሬ ተፈሪ ተከትላ የነሃስ ሜዳልያ አግኝታለች።

  ከዚህ ውድድር አንድ ወር አስቀድሞ በሞናኮ የርቀቱን የዓለምን ክብረ ወሰን በ3 ደቂቃ ከ50 ነጥብ 7 ሰከንድ በመግባት መስበሯም አይዘነጋም።

  ይህ ሪከርዷም እንደ አውሮፓውያኑ ከ1993 ወዲህ የተመዘገበ ምርጥ ስአት ነው።

  አትሌት ገንዘቤ በተጨማሪም በ5 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር በ14 ደቂቃ ከ18 ነጥብ 86 ሰከንድ በመግባት ክብረ ወሰን መስበሯን ማህበሩ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

  ገንዘቤ በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ማህበር የአመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማት ስለተበረከተላት ደስተኛ መሆኗን የገለጸች ሲሆን፥ ባለፈው አመትም ሽልማቱን ለመውሰድ ከጫፍ ደርሳ እንደነበር አስታውሳለች።

  ከሞናኮ እስከ ቤጂንግ የተሳካ የውድድር አመት ማሳለፏን የተናገረችው ገንዘቤ፥ የመረጧትን እና ድጋፍ ያደረጉላትን አካላት አመስግናለች።

  አትሌት ገንዘቤ በ2016 በፖርትላንድ በሚካሄደው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የመሳተፍ እና በዚህ ውድድር የአለም ክብረ ወሰን ለመስበርም በየካቲት ወር በስቶኮልም ውድድር እንደሚኖራት ተናግራለች።

  ምንጭ፡- IAAF

   

  Read more »
 • Ethiopia seek redemption against Somalia

  Ethiopia Walia Ibex coach Yohannes Sahle has his work cut out when they his side plays Somalia in a Group A game at the Hawassa Kenema stadium today.

  Ethiopia, who are the hosts, need a win to give back their adoring fans hope and playing against a Somalia side that conceded four goals against Tanzania.

  “I have urged my players not to underrate Somalia even though they conceded more goals in their first match. We lost narrowly to Rwanda and I believe we have the capacity to make a comeback and still be in contention for the Cecafa title. We are ready for the challenge today and I believe the players will rise up to the occasion and give the fans something to smile about,” Sahle told supersport.com.

  Ethiopia have been rebuilding their team since Sahle took over earlier in the year from the golden generation that played in the 2003 Africa Cup of Nations.

  Read more »
 • CECAFA 2015 ELECTIONS

  President of Sudan Football Association, Dr. Mutasim Gafaar, has been elected the new president of the council of east and central Africa football associations [CECAFA] during the regional Africa football body’s election in Addis Ababa on Friday.

  Four executive committee members have also been elected, while long time servicing Secretary General, Nicholas Musonye [Kenya] will continue his role as secretary General.

  The Executive committee members are:

  Abdiqani Said Arab [Somalia], Alei Ghabur Goc [South Sudan], Souleiman Hassan Waberi [Djibouti] and Habimona Aimable of Burun

   

  Source cecafafootball.org

  Read more »
RSS