Habesha2day
Welcome
Login

Amharic (ኣማርኛ)


Ahmaric Health Tips

 • ለትርፍ አንጀት ችግር ያለው ህክምና ኦፕሬሽን ብቻ ነው. ዶ/ር ኃይሉ አለሙ

  [ሓበሻቱደይ]ትርፍ አንጀት ከስያሜው መረዳት እንደምንችለው ለሰውነታችን አገልግሎት ይሰጣሉ ተብለው በተፈጥሮ ከተሰጡን የሰውነት ክፍሎች መካከል ትርፉ ነው። ይህ ትርፍ አንጀት ብዙዎቻችን እንደምናስበው በአንድ ጊዜ የሚከሰት ሳይሆን ስንፈጠር ጀምሮ አብሮን የሚኖር ነው። የትርፍ አንጀት ችግር አጋጣሚ አግኝቶ ወደ ህመምነት ከተቀየረ ህይወትን እስከማሳጣት ይደርሳል። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ስፔሻሊት ከሆኑት ዶክተር ኃይሉ አለሙ ጋር ቆይታ አድርገን እንደሚከተለው ይዘን ቀርበናል።

  የAppendix ምስል ውጤት

  Read more »
 • ቦርጭ ለመቀነስ የሚረዱ ምክሮች

   

  1.   ቁርስ ይመገቡ፡ ይህ የሚጠቅም አይመስልም ግን በጣም አስፈላጊ ነዉ፡፡ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ከእንቅልፋችን በነቃን በአንድ ሰዓት ዉስጥ ቁርስ መመገብ የኢንሱሊን መጠንን ያረጋጋል፡፡

  • በቁርስ ሰዓት እንደ እንቁላል፣ አቮካዶና የለዉዝ ቅቤ የመሳሰሉ ባለ ከፍተኘ ፋይበር ምግቦችን መመገብ ለመፈጨት ጊዜ የሚወስዱ በመሆናቸዉ ቶሎ እንዳይርበንና በምሳ ሰዓት ብዙ እንዳንመገብ ያግዙናል፡፡ በዚህም ምክንያት የካሎሪ አወሳሰዳችን ይቀንሳል፡፡ 
  •  ጣፋጭ ቁርሶችን ያስወግዱ፡፡ እንደ ኬክ፣ ፓንኬክ እና ፍሬንች ቶስት የመሳሰሉትን ይተዉ፡፡


  2.   ዉጥረትን ይቀንሱ፡ ስንጨነቅና ስንወጣጠር በሰዉነታችን ዉስጥ የሚመነጨዉ ኮሪስቶል የተባለዉ ሆርሞን የቦርጭ ሁኔታን እንደሚያባብስ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ዉጥረትን ለመቀነስ የሚረዱ ጥቂት ስልቶች-

  • በቂ እንቅልፍ ይተኙ፡፡ የእንቅልፍ እጦት የመነጫነጭ ስሜት ከመፍጠሩም ባሻገር በትንሽ በትልቁ እንድንወጣጠር ያደርገናል
  •  ፈታ ለማለት ጊዜ ይመድቡ፡፡ ምናልባትም ከምሳ እረፍትዎ ላይ 15 ደቂቃ ወስደዉ ብቻዎን በመሆን ይመሰጡ (አይኖን በመጨፈን በጥልቁ ይተንፍሱ፤ ዉጥረቶን ለመቀነስ ይሞክሩ)፡፡ የሚያስደስቶትን ነገር ያድርጉ- ሙዚቃ ያድምጡ፣ ሻወር ይዉሰዱ፣ ሻማ ያብሩ፣ ዮጋ ይስሩ ወዘተ
  • የሚያስጨንቁ ነገሮችን ከመኝታዎ አካባቢ ያርቁ! የቢሮ ወረቀት፣ አሳይመንት የመሳሱትን አልጋዎ ላይ ይዘዉ አይዉጡ፣ ትተዋቸዉ መኝታ ቤት ይግቡ፡፡ አይምሮዎ በተወሰነ መልኩ ነፃ ይሆናል፡፡ የሞባይል አላርምን ለመተዉ ይሞክሩ- ምናልባትም ተፈጥሯዊ ከእንቅልፍ የመነሳት ጥበብን (ለምሳሌ መጋረጃ ከፈት በማድረግ በፀሀይ ብርሃን መንቃት) ይለማመዱ፡፡ ሞባይላቸዉን ከመኝታ የሚያርቁ ሰዎች የተሻለ እንቅልፍ ይወስዳቸዋል፡፡ 


  3.  ፈጠን ያለ ወክ ያድርጉ፡ ፈጠን ያለ እርምጃ ማድረግ ቦርጫችንን በእጅጉ እንድንቀንስ ያግዘነል፡፡በተለይም ጂምናዚየም ገብተዉ ለመስራት ጊዜ በማይገኝበት በዚህ ጊዜ ይህ በቀላሉ ልናደርገዉ የምንችለዉ ስፖርት ነዉ፡፡ ሊፍት ከመጠቀም ይልቅ ደረጃዉን በእግር መዉጣት፣ ታክሲ ከመጠቀም በእግር መሄድ (በተለይ ጠዋትና ማታ- እኛ ምን አጋፋን?:)

  4.   ሙሉ ለሙሉ የላሙ ምግቦችን አይምረጡ፡ በየሰፈራችን ተሰልፈን የምንገዛዉ የፉርኖ ዳቦ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ነዉ፡፡ ስንዴ ዉስጥ ያለዉ አስፈላጊ የምግብ ይዘት ተመጦ ያለቀ በመሆኑ ለጤና አይመከረም፤ ይልቁንም ብዙ ሂደት ያልተካሄደባቸዉ እንደ እንጀራና የሐበሻ ዳቦን መምረጥ ተገቢ ነዉ፡፡ 

  5.   ብዙ ዉሃ ይጠጡ፡ ብዙ ዉሃ መጠጣት ቦርጭ ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ነገር ግን ይህ የሚሰራዉ የሚበሉትን ምግብ መጠን ከቀነሱ ነዉ፡፡ በቀን ዉስጥ እስከ 8 ብርጭቆ ዉሃ መጠጣት ከሰዉነተችን መርዛማ ኬሚካሎች እንዲወገዱም ይረዳል፡፡ 

  -    ቤቨሬጅ የሆኑ አልኮሎችን (ቢራ፣ ድራፍት፣ ጠላ፣ ጠጅ…) በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሱ፡፡ ለስላሳዎችን ከቻሉ ይተዉ፤ ቦርጭ ለመቀነስ ብቻ ሳይሆን ለጤናዎም በማሰብ

  6.  ስፖርት ይስሩ፡ ሩጫ፣ ገመድ መዝለል እና ሌሎች የልብ አቅምን የሚያጎለብቱ እንቅስቃሴዎች ማድረግ ቦርጭን ይቀንሳል፡፡ ቦርጨዎ እስኪጠፋ ድረስ ጡንቻን የሚያዳብሩ አንቅስቃሴዎችን አይስሩ ምክንያቱም ቦርጫችን እንዲጠነክር እንጂ እነዲቀንስ አያደርግም 

  7.   የሚመገቡትም ምግብ ይቀንሱ ግን ይህንን ሲያደርጉ የሚመገቡትን ምግብ ጥራት እና ተስማሚነት ያሻሽሉ፡፡ አትክልትና ፍራፍሬን ያዘዉትሩ፡፡

  8.   ጥሩ የፋት ምግቦችን ይመገቡ፡ እንደ አቮካዶ፣ ለዉዝ እና ስኳር የሌለዉ ጥቁር ቸኮሌት ሆዳችን አካባቢ ቦርጭ እንዳይከማች ይረዳሉ፡፡ በተቻሎት መጠን እነደ ማርጋሪንና ኩኪስ የመሳሰሉ ምግቦችን ያስወግዱ- ቦርጭን ያባብሳሉ፡፡

  9.   ቦርጭ ያለዉን ጉዳት ያስቡት፡ በዋነኝነት ቦርጭ መቀነስ የሚገባን አምሮብን እንድንታይ ሳይሆን የጤና ጉዳት ስላለዉ ሊሆን ይገባል፡፡ የልብ ህመም እና ስኳር የመሳሰሉ ህመሞች ቦርጭ ይመቻቸዋል፡፡ ስለሆነም በቅድሚያ ስለጤናችን ብለን ቦርጫችንን ለመቀነስ ከሰራን ዉበቱ ከዚያ አብሮ ይመጣል

  ተጨማሪ ምክሮች
   ዉሃ ከምግብ በፊትና በኋላ ይጠጡ፡፡ ከምግብ በፊት የሚጠጡት ሆዶን ስለሚሞላሎት ብዙ እንዳይበሉ ይረዳዎታል፡፡ በኋለ የሚጠጡት ሆድ እቃዎን ያፀዳሎታል

  • አንድን ምግብ ከመመገብዎ በፊት ለምን ሊበሉ እንደሆነ ያስቡ፡፡ እዉን ርቦት ነዉ ወይስ 6፡00 ወይም 6፡30 ሆኖ የምሳ ሰዓት ስለደረሰ ነዉ የሚበሉት? ካልራበት በቀር ምግቡን አይብሉት፡፡ የመመገብ ዉሳኔያችንን ለሆዳችን እንጂ ለጭንቅላታችን አንስጠዉ፡፡ 
  •  ገመድ መዝለል ከሩጫ በላይ ቦርጭን ያጠፋል
  •   በዛ ያለ ቁርስ፣ መለስተኛ ምሳና ትንሽዬ እራት ይመገቡ፡፡ ለዉጡን ያዩታል፡፡
  Read more »
 • የሙዝ ጥቅሞች

  ሙዝ በውስጡ የካርቦሃይድሬት ንጥረነገሮችን የያዘ በመሆኑ ከፍተኛ ሃይል እንድናገኝ ይረዳናል። ሁለት ሙዝ በልተን በምናገኘው ሃይል ለዘጠና ደቂቃ አድካሚ የጉልበት ሥራዎችን መሥራት እንደምንችል ዶ/ር ታዬ ይናገራሉ፡፡ ብዙዎቻችን ሙዝን ለምግብነት በማዋል ለሰውነታችን ሃይልና ሙቀት ለማግኘት እንደምንችል ከማወቅ የዘለለ ነገር አስበን አናውቅም፡፡ ነገር ግን ሙዝ በውስጡ የያዛቸው ተፈጥሮአዊ የስኳር ወይም የጣፋጭ ምንጭ የሆኑት ግሉኮስ፣ ስክሮስ፣ እና ፍሩክቶስ የተባሉት ንጥረነገራት ከሙዝ የፋይበር (የቃጫነት) ተፈጥሮ ጋር ተዳምረው መጠነሰፊ ጠቀሜታዎችን ይሰጣሉ። ከበርካታ የሙዝ ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን ከዚህ እንደሚከተለው ለማየት እንሞክራለን፡፡ 

   

  1. ለአእምሮ እድገት 

  ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ የፖታሺየም ንጥረነገርን ይዟል፡፡ ይህም ንጥረ ነገር የአንጐልን የሥራ ብቃት ለማሻሻል እና ለማሳደግ እንዲሁም ንቁና ጤናማ አዕምሮ እንዲኖረን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ 
  2. ለስትሮክ 
  በሙዝ ውስጥ ያለው ፖታሺየም፣ የደም ሥርዓትን በማስተካከል ባልታሰበ ሁኔታና በድንገት የሚከሰተውን የስትሮክ ችግር ለመከላከል ያግዛል። ሙዝ በሰው ልጆች የአመጋገብ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ ዘወትር ለምግብነት የሚውል ከሆነ፣ በስትሮክ ምክንያት የሚመጣውን ድንገተኛ ሞትና የአካል ጉዳት ከ50-60 በመቶ ለመቀነስ ያስችላል፡፡ 

  Read more »
 • ኤች አይ ቪ ኤድስን ለማጥፋት የተሳካው ሙከራ ተገኘ !

   

  * ጠቢባን ወደ አበረታች ጠቃሚ ግኝት መሸጋገራቸው እየተነገረ ነው 
  * ቀሳፊው የኤድስ ህዋስን ለይቶ ለማውጣት የሚያስችል ጥበብ ተገኝቷል 
  * ፈውሱን ወደ ታካሚዎች የማውረዱ ስራ ገና አልተጀመረም

  አንዴ ከሰው ልጅ ጤነኛ ህዋስ ጋር ከተጣበቀ መለያየት የማይችለው የ HIV ኤች አይ ቪ ኤድስ በአለም ፈውስ ካልተገኘላቸው በሽታዎች ሆኖ የአንድ ጎልማሳ እድሜ አሳልፈናል።

  ሁለት አስርት ዓመታት በዘለቀው የቀሳፊው HIV በሽታ ጉዞ ከ3 ሚሊዮን ያላነሱ ሰዎች በበሽታው ሲጠቁ እልፍ አዕላፍ ዜጎች ተቀስፈዋል። ምንም እንኳን በሁለት አስርት አመታቱ የቀሳፊው ጉዞ ህዋሱን ከተጣበቀበት ጤነኛ ህዋስ ጨርሶ ማለያየት ባይቻልም ማቆያ የሚሆን መድሃኒት ግን አልጠፋም ።

  Read more »
 • ኩላሊትን የሚጎዱ ነግሮችና እና የኩላሊት በሽታ ምልክቶች!!!

    ኩላሊትን የሚጎዱ ነግሮችና እና የኩላሊት በሽታ ምልክቶች!!!

  ኩላሊት(ቶች) የምንለው ሁለት ልክ እንደ ባቄላ አይነት ቅርጽ ያላቸው በሁለቱ የሰውነታችን ጎኖች የሚገኙ ከደም ውስጥ ቆሻሻን ለማስወገድ, የሰውነታችንን የፈሳሽ መጠን ለማስተካከል እንዲሁም ሌሎች የሰውነት ስራዎችን የሚያግዝ(ዙ) የሰውነታችን ክፍል ነው::

  ከላይ እንደተጻፈው አንድ ሰው ጤነኛ ሆኖ ለመቆየት እና ለመኖር የኩላሊቱን ጤንነት መጠበቅ ይኖርበታል::

  ከታች የተዘረዘሩት በቀላሉ የኩላሊት በሽታን ሊያስከትሉና ልንጠነቀቃቸው የሚገቡ ባህሪያት ናቸው::

  1. ሽንትን መቋጠር
  2. በቂ ውሃ አለመጠጣት
  3. ጨው የበዛበት ምግብ መመገብ
  4. ኢንፌክሽኖችን በተገቢው ሁኔታና በቶሎ አለመታከም
  5. የስጋ አመጋገብን ማብዛት
  6. በቂ ምግብ አለመመገብ
  7. ለሕመም ማስታገሻ ተብለው የተሰሩ መድኃኒቶች አብዝቶ መጠቀም
  8. ለብዙ ግዜ የቆየ የኢንሱልን ተጠቃሚነት
  9. የአልኮል መጠጥ
  10. በቂ እረፍት አለማግኘት

  የኩላሊታችንን ጤንነትን መጠበቅ አቅቶን ለኩላሊት በሽታ ከተጋለጥን በፍጥነት በአቅራቢያ ወደሚገኝ የህክምና ማዕከል በመሄድ አስፈላጊውን ሕክምና ማግኘት ይኖርብናል::

  የኩላሊት በሽታ ምልክቶች : -
  • የእጅና የእግር እብጠት
  • መዳከምና አቅም ማጣት
  • ለመትንፈስ መቸገር
  • የተደጋገመ ትውከት
  • የምግብ ፍላጎት መቀነስ
  • ለነገሮች ትኩረት (concentration) አለመስጠት
  • አፍችን ውስጥ የብረት ጣዕም(ስሜት) መሰማት

  ኩላሊታችን ሙሉ ለሙሉ መስራት ካቆመ ያለው መፍትሄ የኩላሊት እጥበት ሲሆን ከዚህ ካለፈ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ሊያስፈልገን ይችላል::

   

   

  Read more »
RSS