Habesha2day
Welcome
Login

Amharic (ኣማርኛ)


Ahmaric Health Tips

 • የስንፈተ ወሲብ – ከ10 በላይ ምክንያቶችና ከ10 በላይ መፍትሄዎች

   

  በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት የሚፈጠር ችግርን በግልፅ ተነጋግሮ፣ መፍታትን ባህሉ ባደረገ ማህበረሰብ ውስጥ የስንፈተ ወሲብ ችግር የትዳር አደጋ የመሆኑ ጉዳይ ብዙም አሳሳቢ ላይሆን ይችላል፡፡ሀገራችንን ጨምሮ በአፍሪካና በኤዢያ በትዳር ተጣማሪዎች መካከል በግልፅ የመነጋገር ባህል የዳበረ እንዳልሆነ በስነ ማህበረሰብ ሙያተኞች የተጠኑ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ ስንፈተ ወሲብ ፆታና ዕድሜ ሳይለይ ይከሰታል፡፡ አደጋ የሚሆነው ችግሩ መከሰቱ ሳይሆን፣ ጥንዶች በተፈጠረው ችግር ዙሪያ በግልፅ ተወያይተው መፍትሄ ለማፈላለግ ዝግጁ አለመሆናቸው ነው፡፡

  በፍቅረኞችም ሆነ በባለትዳሮች መካከል የሚፈፀም ወሲብ፣ ለሁለቱም የእርካታ (የደስታ) ምንጭ መሆኑ ሲቀር ‹‹ለምን?›› ብለን መጠየቅም ሆነ ርዕሰ ጉዳዩን በጠረጴዛ ዙሪያ አምጥቶ አለመነጋገር ብዙዎቻችን አንደፍርም፡፡ ፈቃደኝነቱም የለንም፡፡ ችግሩ እየተባባሰ ሲመጣ፣ ግንኙነቱ በፍቅረኝነት ደረጃ ላይ ያለ ከሆነ በቃሽኝ (በቃኸኝ) በሚል ይቋረጣል፡፡ ትዳር ከሆነም የፍቺ ጥያቄ ማቅረብ በሀገራችን የተለመደና በየጊዜው ቁጥሩ እየጨመረ የመጣ ክስተት ሆኗል፡፡ የሚገርመው ግን በፍቅረኞች (በትዳር) ደረጃ የተመሰረተው ግንኙነት፣ በአንድ ጀንበር ለማፍረስ ሲወሰን እውነተኛው ምክንያት ከመጋረጃ ጀርባ የተደበቀ ነው፤፤ ፍቺ የጠየቀችው ሴቷ ከሆነች ‹‹ይሰክራል፣ ይደበድበኛል፣ ገንዘብ ይደብቀኛል፣ ከእኔ ሌላ ሴት ወዷል ወዘተ…›› በሚል የውሸት ጭንብል ትሸፍነዋለች፡፡ የትዳር ይፍረስ ጠያቂው ወንዱ ከሆነ ደግሞ ‹‹ትጨቀጭቀኛለች፣ ገንዘብ ታባክናለች፣ ከእኔ ይልቅ የምትሰማው ወላጆቿን ነው ወዘተ…›› በማለት ለግንኙነቱ መሻከር ቁልፍ ምክንያት የሆነውን ችግር ወደ ጎን ሲገፋው ይስተዋላል፡፡ ‹‹ችግሩን የደበቀ መድሃኒት አያገኝም›› እንደሚባለው፣ የስንፈተ ወሲብ ጉዳይን በሀገራችን ባህል ለውይይት የማይቀርብ አጀንዳ በመሆኑ፣ የብዙ ትዳሮችን መፍረስ ከመጋረጃ ጀርባ ያለ አብይ ምክንያት ሆኖ ዛሬም ድረስ ቀጥሏል፡፡

  በዘርፉ ጥናት ያካሄዱ ሙያተኞች ስንፈተ ወሲብ መፍትሄ ያለው የስነ ልቦና፣ የአካላዊና የአዕምሯዊ ጤና ችግሮች ውጤት ነው ይላሉ፡፡ በዛሬው ዝግጅት የስንፈተ ወሲብ ችግር ምንነትን፣ መንስኤን፣ አጋላጭ ምክንያቶችን፣ በሀገራችንና በዓለም ላይ ያሉ አማራጭ መፍትሄዎችን እንደዚሁም ከርዕሰ ጉዳዩ ጋር በተያያዘ፣ መታወቅ አለባቸው በምንላቸው ሐሳቦች ዙሪያ፣ ሙያዊ ማብራሪያ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

  ጥያቄ፡- ስለስንፈተ ወሲብ ችግር ምንነት፣ የተወሰነ አጠቃላይ ሐሳብ ብናነሳና ውይይታችንን በዚሁ ብንጀምረው ጥሩ ይመስለኛል?ዶ/ር፡- ስንፈተ ወሲብ የሚለውን ቃል፣ ጠበብ ባለው ዐውዱ ሲታይ፣ የወንድም ሆነ የሴት ብልት አለመነቃቃትንና ለግንኙነት ዝግጁ ካለመሆን ጋር የቀጥታ ቁርኝት ያለው ነው፡፡ ነገር ግን ስንፈተ ወሲብ ብልት ለግንኙነት ዝግጁ አለመሆን ማለት ብቻ አይደለም፡፡ ከዚህም ሰፋ ያለ ትርጓሜ ያለው ነው፡፡ የስንፈተ ወሲብ ችግር በሁለት መንገድ የሚከሰት ነው፡፡ የመጀመሪያው ተፈጥሯዊ በሆነ የአፈጣጠር ችግር ማለትም በክሮሞዞን፣ የሴትነትና የወንድነት መገለጫ በሆኑት የኦቫሪና የቴስትሮን አፈጣጠር ችግር ምክንያት የሚፈጠር ሲሆን፣ ሁለተኛው ከውልደት በኋላ በዕድገት ሂደት በአካላዊ፣ በአዕምሯዊ፣ በስነ ልቦናዊና በአካባቢያዊ ምክንያቶች የሚፈጠር የስንፈተ ወሲብ ችግር ነው፡፡ በዚህ ወቅት የሚፈጠረው ችግር ለግብረ ስጋ ግንኙነት ፈፅሞ ዝግጁ አለመሆንን፣ ጭራሹኑ ስሜት ማጣትን፣ ፍላጎት አለመኖርን፣ የመጨረሻው እርካታ ላይ አለመድረስን፣ የሌላኘውን ስሜት ሳይጠብቁ ፈጥኖ መርካትን፣ ለግንኙነት ዝግጁ ያለመሆንን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

  Read more »
 • ራሰ በራነት ምንድን ነው?መነሻው እና ህክምናው ምንድን ነው?

    

  ፀጉር በማንኛውም የሰውነታችን ቆዳ ላይ ከእጃችን መዳፍ እና ከእግራችን ሶል ዉጪ ይበቅላል ነገር ግን አብዛኛዎቹ ፀጉሮች ስስ ስለሆኑ በአይናችን ላናያቸው እንችላለን፡፡ ፀጉር ኬራቲን() ከሚባለው ፕሮቲን በዉጨኛው የቆዳ ክፍል የፀጉር ፎሊክል ዉስጥ ይሰራል፡፡ ፎሊክላችን አዲስ የፀጉር ሴል ሲሰራ/ሲያመርት አሮጌ ሴሎቻችን በአመት 6 ኢንች ወደ ዉጪ ቆዳችን ተገፍተው ይወጣሉ የምናየው ፀጉር የሞተ ክር መሳይ ኬራቲን ሴል ነው፡፡ በአማካይ የአንድ አዋቂ ሰው ጭንቅላት ከ 100000-150000 የሚደርስ ፀጉር ሲይዝ በቀን 100 ፍሬ ፀጉር በራሳቸው ጊዜ ይነቀላሉ በማበጠሪያች ውስጥ ትንሽ የተነቀሉ ፀጉር ማግኝት የተለመደ እና ሊያስደነግጠን የማይገባ ጤናማ ሁኔታ ነው፡፡

  ፀጉር እምራች የሆኑት እያንዳንዳቸው ፎሊክሎች የራሳቸው የሆነ የእድሜ ገደብ ሲኖራቸው በእድሜ፣ በበሽታ እና በተለያዩ በርካታ ምክንያቶች ተጽእኖ ይወሰናሉ፡፡ ይህ አውደ ህይወት በሶስት የለውጥ ደረጃ ይከፈላሉ

  1.አናጅን ፦ ፀጉር በፍጥነት የሚያድግበት ጊዜ ሲሆን ከ2-6 ዓመት ያበቃል
  2.ካታጂን፦ ይህ የፀጉር እድገት ጊዜ የሽግግር ደረጃ ሲሆን ከ2-3 ሳምንት ይፈጃል
  3.ቴሎጂን፦ የእድገት ጊዜ የሚያርፍበት/የሚቆምበት ሲሆን ከ2-3 ወር ይፈጃል፡፡ በዚህ የለውጥ ደረጃ መጨረሻ ላይ ፀጉራችን ይረግፍና የዕድገት ሂደቱን እንደገና ከመጀመሪያ ይጀምራል፡፡

  እድሜያችን እየጨመረ ሲሄድ የፀጉር እድገት ፍጥነቱን ይቀንሳል፡፡ ፀጉራችንን የምናጣበት በርካታ ዓይነቶች አሉ እነሱም

  አንድሮጀኒክ አሎፔሺያ
  ወንድና ሴትን የሚያጠቃ በዘር ህዋስ ምክንያት የሚከሰት ነው፡፡ ወንዶች በወጣትነታቸው ወይም በሃያዎቹ መጀመሪያ ፀጉራቸው ያሳሳል፡፡ በመሃልና በፊት ጭንቅላታቸው ላይ ያሉ ፀጉሮች ቀስ በቀስ ያሳሳሉ፡፡ ሴቶች እድሜያቸው 40 እስከሚሆን የፀጉር መሳሳት አይታይባቸውም፡፡ ሴቶች አጠቃላይ በጭንቅላታቸው ላይ ያለ ፀጉር ይሳሳል በተለይ መሀል አካባቢ፡፡

  አሎፔሺያ አርያታ
  በድንገት የሚጀምር ሲሆን በመጠንም ሆነ በአይነት ያልተስተካከለ ፀጉርን ማጣት በህፃናት እና ወጣቶች ላይ ያጋጥማል፡፡ ሙሉ ለሙሉ የፀጉር መመለጥ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ በዚህ ሁኔታ ከተጠቁት 90 የሚሆኑት ሰዎች በጥቂት አመታት ውስጥ ፀጉራቸው ተመልሶ ይበቅላል፡፡

  Read more »
 • የኪንታሮት ህመም (ሄሞሮይድስ)

   የኪንታሮት ህመም በታችኛ የትልቁ አንጀትና ፊንጥጣ አካበቢ ያሉ የደም መልስ( veins) የደም ቧንቧዎች በሚያብጡበትና በሚቆጡበት ወቅት የሚከሰት የህመም አይነት ነዉ፡፡ የኪንታሮት ህመም ሰገራ በሚወጡበት ወቅት ሲያምጡ፣ ወይም በፊንጥጣና በታችኛዉ የትልቁ አንጀት አካበቢ ባሉ የደም ስሮች ላይ እንደ እርግዝናና ሌሎች ጭነትን ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮች በሚኖሩበት ወቅት የሚከሰት ነዉ፡፡ ኪንታሮት በታችኛዉ የትልቁ አንጀት ዉስጥ የሚገኙ የዉስጠኛዉ ኪነታሮት(internal hemorrhoids) ወይም በፊንጥጣ ዙሪያ ባለዉ ቆዳ ስር የሚታይ የዉጨኛዉ ኪንታሮት (external hemorrhoids) አይነት በመባል በሁለት ይከፈላል፡፡

  የህመሙ ምልክቶች
  • የኪንታሮት ህመም ምልክቶች እንደኪንታሮቱ ቦታ የሚወሰን ሲሆን የዉስጠኛዉ የኪንታሮት አይነት ብዙዉን ጊዜ በአይን የማይታይ ቢሆንም በሚፀዳዱበት ወቅት ማማጥ ካለዎ የደም ስሮቹ ሊቆጡና በቀላለ ሊደሙ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ በሚያምጡበት ወቅት የዉስጠኛዉ ኪንታሮት አይነት ወደታች በመምጣትና በፊንጥጣ ዉስጥ በማለፍ ህመምና የመቆጥቆጥ ስሜት ሊኖረዉ ይችላል፡፡
  • የዉጪኛዉ የኪንታሮት አይነት በፊንጥጣ ዙሪያ ባለዉ ቆዳ ስር የሚገኝ ሲሆን የደም ስሮቹ በሚቆጡበት ወቅት ሊያሳክኩ ወይም ሊደሙ ይችላሉ፡፡ አንዳንዴ ደም በዉጭኛዉ ኪንታሮት ዉስጥ በመጠራቀምና በመርጋት ከፍተኛ ህመም፣ እብጠትንና መቆጣትን/መለብለብን ሊያመጣ ይችላል፡፡
  • በሚፀዳዱበት ወቅት/ሰገራ በሚወጡበት ወቅት ከፊንጥጣ የሚወጣ ህመም የሌለዉ ደም/መድማት፡- ይህን ክስተት በመፀደጃ ሳህን ላይ ወይም በሶፍት ላይ ሊያዩ ይችላሉ፡፡
  • በፊንጥጣ አካባቢ የማሳከክ ወይም የማቃጠል ስሜት ካለዎ
  • በፊንጥጣ አካባቢ ህመም ወይም ምቾተ ያለመሰማት ካለዎ
  • በፊንጥጣ ዙሪያ እብጠት ካለዎ
  • የሰገራ ማምለጥ ካለዎ

  Read more »
 • ለኩላሊት ጤንነት የሚጠቅሙ 6 ምግቦች

  ጤነኛ ኩላሊት ማለት ልክ እነደ ልብ ጥቅም አለው፡፡ ኩላሊት በሰውነታችን ውስጥ የሚመረቱ፣ የማይፈለጉ፣ ከመጠን በላይ የበዙ እና መርዛማ የሆኑ ነገሮችን ከደማችን በማጣራት በሽንት መልክ ከሰውነታችን ያስወጋዳል፡፡ በተጨማሪም ኩላሊት በሰውነታችን ውስጥ ያሉትን የኔጌቲቭ ቻርጅ መጠን እና የተለያዩ ፈሳሾችን መጠን ይቆጣጠራል፡፡ጤናማ ያልሆነ ኩላሊት የሚከተሉት ችግሮች ያመጣል፡፡ እነሱም፦

  • ሽንት የመሽናት ችግር
  • በአይን አካባቢ እብጠት መፈጠር
  • የእግር እና እጅ ማበጥ
  • ከብዙ ጊዜ በኋላ የልብ ችግር ያመጣል
  • ንጽህናው የተጠበቀና ለጤንነት ጥሪ የሆነ ምግብ መመገብ በሰውነታችን ጤንነት እንዲሁም በትክክል ስራውን እንዲሰራ ያደርጋል፡፡
  • በአብዛኛው አንቲ ኦክሲዳንት(Antioxidant) የሆኑ ምግቦች ለምሳሌ፦ እንደ ፍላቮኖይድስ(Flavonoids)፣ ሊኮፔን(Lycopene)፣ ቤታ-ካሮቲን(Beta-carotene) እና ቫይታሚን ሲ(Vitamin C) ንጥረ ነገሮችን የያዙ ምግቦችን የኩላሊት ጤንነትን ይጠብቅልናል፡፡
  • አንቲ ኦክሲዳን(Antioxidant) በሰውነታችን ላይ የሚካሄደውን ኦክሲዴሽን(Oxidation) በነፃ ኤሌክትሮን እነዚህ ትርፍ ወይም ነፃ ኤሌክትሮን ዋናው በኩላሊት በሽታ መንስኤ ነው፡፡
  6 ለኩላሊት ጤንነት የሚጠቅሙ ምግቦች እነሆ፦

  1. ጥቅል ጎመን

  ጥቅል ጎመን የኩላሊት ስራን ያፋጥናል በተጨማሪም ኩላሊትን በመጠገንና ስራውን አቀላጥፎ እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡ የኩላሊት ችግር ያለባቸው ሰዎች ጥቅል ጎመንን እንዲመገቡ ይመከራል፡፡

  2. ቤሪስ/ፍራፍሬ(Berries)

  የማንጋኒዝ፣ ቫይታሚን ሲ፣ ፋይበርና ፎሌት በጣም ጥሩ ምንጭ ነው፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ የቤሪስ ፍራፍሬዎች እንጆሪ፣ ክሬን ቤሪስ፣ ራስፕ ቤሪስ፣ እና ብሉ ቤሪስ ለኩላሊት ጥሩ ናቸው፡፡ቤሪስ ፀረ ኦክሲዳንት እና ኢንፍላሜሽን ባህሪ አላቸው ስለዚህ የሽንት ፊኛ ተግናሩን በትክክል እንዲወጣ ያግዙታል፡፡ እነዚህ የቤሪስ ፍሬዎችን ወዲያው የተቆረጡ(ትኩስ)፣ የቀዘቀዙ ወይም ደረቅ መጠቀም ሲቻል በጥሬው መመገብ ወይም በመደበኛ የምግብ ዝርዝር ውስጥ በማስገባት መጠቀም ተመራጭ ነው፡፡

  Read more »
 • ሲያጌጡ ..... ብርሃንዎን እንዳያጡ!

  http://www.mahderetena.com/amharic/wp-content/uploads/2015/05/f956f9f356510b46ab586764cee0d1fe_M.jpg

  ለሃኪም ትዕዛዝ የሚደረጉ መነፅሮች ለአይነስውርነት ሊያጋልጡ ይችላሉ::
    ፒያሣ ነኝ፡፡ ሲኒማ ኢትዮጵያ ፊት ለፊት፤ ቼንትሮ ካፌ ጀርባ ከሚገኘው የደራ የመነፅር ገበያ ውስጥ። እዚህ መነፅር ለመግዛት ከየሥፍራው የሚመጡ በርካታ ወንድና ሴት ወጣቶችን ማግኘት ይቻላል። ቦታው ሁሉም እንደየምርጫውና እንደየአቅሙ የሚፈልገውን ማግኘት የሚችልበት ሥፍራም ነው፡፡ ሸማቹ አይኑ የገባችውን መነፅር ያስወርድና አይኑ ላይ ስክት አድርጎ በትንሿ ክብ መስታወት አየት አየት ያደርግና ከሻጩ ጋር ዋጋ ይደራደራል፡፡ በዋጋ ድርድሩ ከተስማሙ ዋጋዋን ከፍሎ መነፅሯን ይዞ ይሄዳል፡፡ የንባብ፣ የፀሐይ፣ የዝነጣ፣ የዋና እና የልጆች እየተባሉ የሚለዩ የመነፅር አይነቶች በብዛትና በዓይነት ለሽያጭ ከሚቀርቡባቸው የከተማዋ የንግድ ቦታዎች የፒያሳው የመነፅር ገበያ ዋንኛው ነው፡፡ ከ70 ብር ጀምሮ እስከ ስድስትና ሰባት ሺህ ብር ዋጋ የወጣላቸው መነፅሮች ለገበያ የሚቀርቡበት ሥፍራም ነው፡፡ ያለ ሃኪም ትዕዛዝ በግምትና በውበታቸው ብቻ እየተገዙ በጥቅም ላይ የሚውሉት እነዚህ የዓይን መነፅሮች ግን ለከፋ የጤና ችግር ሊዳርጉና ለአይነስውርነትም ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

  ለመሆኑ መነፅር ማድረግ የሚያስፈልገን መቼ ነው? ምን ዓይነት መነፅርስ ነው የምናደርገው? ለአቧራና ለፀሐይ መከላከያ እየተባሉ ያለ ሃኪም ትዕዛዝ ከየገበያውና ከየሱቁ እየተገዙ ጥቅም ላይ የሚውሉት መነፅሮች የሚያስከትሉት የጤና ችግር ምንድነው? አንድ ሰው የእይታ ችግር ገጥሞታል የምንለው መቼ ነው? በርቀት ወይም በቅርበት የማየት ችግር ስንልስ ምን ማለታችን ነው?
  በዓለም ጤና ድርጅት መመዘኛ መሰረት አንድ ሰው በሁለቱም አይኖቹ ከሶስት ሜትር ርቀት ላይ ጣት መቁጠር ካልቻለ ዓይነስውር ነው፡፡ በዓለማችን 2.3 ቢሊዮን የሚሆኑ ህዝቦች ከእይታ መድከም ጋር የተያያዘ ችግር እንዳለባቸውና ከዚህም ከፍተኛውን ቁጥር የያዙት የእስያ አገራት ህዝቦች መሆናቸውን ይኸው የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ከጥቁር ህዝቦች ይልቅ ነጮቹ፣ በፆታ ደግሞ ከወንዶች ይልቅ ሴቶቹ በርቀት ለማየት ችግር የተጋለጡ መሆናቸውንም መረጃው ጨምሮ ገልጿል፡፡

  Read more »
RSS