Habesha2day
Welcome
Login

Amharic (ኣማርኛ)


Ahmaric Health Tips

 • Every ending implies a new beginning(ማንኛውም መጨረሻ አዲስ ጅምርን ያመለክታል)

  ሰው እስከሆንክ ድረስ ፤ ሰው የመሆን መለያ እስከተሰጠህ ድረስ እንከኖች አይጠፉም። ሰው እስከሆንክ ድረስ የህልውናህ ክብር በማስመልከት ራስህን የመግዛትና አንተነትህን በራሱ ሀይል የበለጠ እውን ለማድረግ የምትችል ፍጡር እስከሆንክ ድረስ እንከኖች አይጠፉም። ምናልባት እንከኖቹ ያንተው የመጨረሻ ሊመስሉህ ይችላሉ ዳሩ ግን ሌላ ነው። የመጨረሻው ጫፍ ስትደርስ ያንተው ሌላ መጀመርያ ሂደት ነው። ለምን ቢባል ማንኛውም መጨረሻ አዲስ ጅምርን ያመለክታል። ማንኛውም መጀመርያ የታላቅ መንገድ መነሻ ነው። ይህ መንገድ ፍፁም አያልቅም። እንደ ሁሉም መንገድ ማለትም ቅፅበታዊ ፍርሀት ፣ ደስታ ፣ ሰላም ፣ ሀዘን ፣ አመፅ ፣ ስጋት ፣ ተስፋ ማንኛውም ጥልቅ ስሜት ካንተ ውስጥ በሐሳብ የተሰሩ ናቸው። ይህም ያንተው ህይወት ነው። ልትቀበለው ይገባል።

  Read more »
 • ወንዶችን የወሲብ ስሜት የሚያቀዘቅዙ ደርጊቶች

  1. ወሲብ እንደማይወድ ሆነው የሚቀርቡ ሴቶች

         የእነዚህ ሴቶች ባህሪና የሚያቀርቡት አስተያየቶች፡

  -      ወሲብ ስሜት እንደማይሰጥና አዋራጅ አድርገው ያቀርባሉ

  -      ስለወሲብ ሲወራ ያፍራሉ

  -      ወሲብ ከፈፀሙ በኋላ እኔና አንተ ያደረግነው ነገር ለማንም እንዳትናገር ወሲብ የፈፀምኩት ላንተ ብዬ   ነው ይላሉ፡

  በነዚህ ምክንያት በሷ ያለው የወሲብ አመለካከትና ቀረቤታ ይቀዘቅዛል። እዚህ ላይ ሊጠነቀቁ ይገባል የሚወዱትን ወንድ ላለማጣት ሲሉ። እያንዳንዱ ድርጊት ፈቅደውና ደስ ብሏቸው እንዳደረጉት ከውስጦ ማመን አለባቸው።

  2. ወሲብ በጭራሽ የማያነሳሱ ሴቶች

  እነዚህ ሴቶች በወሲብ ወቅት የራሳቸውን ድርሻ አለመዋጣት ማለት ነው። ምንም ስሜትን አለመስጠት ለወንዱ የወሲብ ሲሜቱ ቀዝቃዛ ያደርጋል። እንዴት ስለ ወሲብ ማወቅ እንዳለባቸው ከጓደኞቻቸው አልያም ከባለሞያ ጋር መምከር አለባቸው።

  3. የወንዱን ሰውነት እንደማያውቁ ሁነው መቅረብ ማለትም እንደ የወንድ ብልት ምን መሆኑን ሆን

  ብለው የማያቁ መምሰል፤

  ይህ ደግሞ ወንዱን በቀላሉ ሲሜቱ ያቀዘቅዘዋል፤ ይሄን ችግር አስወግደው ስሜትን እንዴት ማነሳሳት እንዳለባቸው ከወዲሁ ይጀምሩ።

  Read more »
 • ለምንድን ነው ብዙ ትዳሮች መጨረሻቸው ፍቺ የሚሆነው?

   

  በአሁኑ ሰዓት የፍቺ መንስኤ ብዙ ቢሆንም እንደ ቀደምት ጊዝያትም 'ትዳር ክቡር ነው' የሚለው የአነጋገር ዘይቤ በሂደት እየቀነሰ መጥቷል። ስለ ትዳር ስናወራ (በዘፍጥ. 1፡26-28) ላይ የእግዛብሔር ስራና እንዲሁም ስለ አዳምና ሔዋን አፈጣጠር ብሎም “….. ብዙ ተባዙ ምድርን ሙሉአት….። ይለናል። ቀጥሎም (በዘፍጥ. 4፡1) ላይ “አደምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ ጸነሰችም ፣ ቃየንንም ወለደች። እርሷም ወንድ ልጅ ከእግዛብሔር አገኘሁ አለች።” ይለናል ይህ የመጀመርያና የመጀመርያው የአብሮነት ኑሮና ቤተሰባዊ ምስረታን ፈርቀዳጅ መሆኑን ያስረዳናል። እንግዲህ መነሻችን ይህ ከሆነ ትዳር ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ በጥልቀት እንዳስሳለን። ትዳር ምንም እንኳን የተለያዩ ብዙ ትርጉሞች ቢሆሩትም አጠር ባለ አገላለጽ ግን ትዳር ማለት በሁለት ተቃራኒ ጾታዎች ማለትም በወንድና በሴት መሃከል  የወሲብና እንዲሁም የአብሮነት አስተሳሰብ ፣ የመቻቻልና የማህበረ-ቁጠባ ተራክቦት በአንደነት ተጋርቶ እስከ እድሜ ፍፃሜ መኖር ማለት ነው።

  በተጨማሪም ካርልፍሬድ ብሮድሪክ(1984) የተባሉ የዩናትድ ስቴት የቀድሞ የናሽናል ካውንስል የቤተሰባዊ ግኑኝነት ፕሬዝዳንት የነበሩ ሲሆኑ ትዳርን በተመለከተ የተለያዩ መግለጫዎች ሰጥተውታል።

  ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹን እንመለከታለን፤

  • ትዳር በሕብረተሰቡ ውስጥ ትልቅ ጉዳይ ሁኖ በያንዳንዱ አከባቢ ማህበራዊ ቡድን ለመፍጠር ያስችለናል።
  • ትዳር ማለት ወንድና ሴትን ማያያዝ የሚችልና ብሎም የሁለቱ ተጋቢዎች የቤተሰብ ቁርኝት የሚፈጥር ነው።
  • ትዳር በሁለቱ ተጣማሪዎችና በሃገሪቱ መሃከል ሕጋዊ ውል ነው። ይህ ማለት ሃገሪቱ ለተጣመሪዎቹ ተፈላጊውን መብትና ሀላፊነት በግልፅ ስለምታስቀምጥ በዝያ መሰረት ደሞ ተጋቢዎቹ ሕጋዊ ውል ይፈጽማሉ።
  • ትዳር የጋራ የገቢ ምንጭ ነው። የጋራ የገቢ ምንጭ ስንል ደግሞ እያንዳንዳቸው ገመጋባታቸው በፊት የራሳቸውን የሆነ ገቢ ይዝው ባንድ ሲጠቀቃለሉ የጋራ ስለሚሆን፤    
  • ትዳር  የተለመደና የተረጋጋ ስሜት ስለሚፈጥር ከለሎቹ ዕድሜ ክልል ውስጥ በዋናነት በአዋቂዎች ላይ ይዘወተራል፤
  • ትዳር ተጋቢዎች ልጆች የሚወልዱበትና ወልደው የሚስሙበት ፤ ብሎም የተለያዩ የማህበራዊ ጉደዮ ላይ በንቃት የሚሳተፉበት ነው።

  በአጠቀቃላይ ከላይ የተገለጹትን የትዳርን ትርጉም ይህን ካልን ለምንድን ነው ታድያ ብዙ ባለ ትዳሮች መጨረሻቸው ፍቺ የሚሆነው? የሚለውን ስንመለከት ደግሞ ፍቺ በተያዩ ምክንያቶች ሚፈጠር ቢሆንም ከታች የምናያችው ግን ዋነኛዎች ለፍቺ ቦታ ይይዛሉ።

  1.  ብዙ ሰዎች ወደ ትዳር ሲገቡ ሐቃዊ ያልሆነ ወይም ይልተረጋገጠ ጥቅም ስለሚጠብቁ። ለምሳሌ የሀብት ክምችት ፣ ቤት ንብረት ወዘተ…። በዚህ ወቅት ያንን ያሰቡት ጥቅም ሳይኖር ሲቀር መጨረሻው ፍቺ ይሆናል።
  2.  የምናገባው ሰው ለተሳሳተ ጥቅም ወይም ምክንያት ማዋል። ለምሳሌ ልጅን ለመውለድ ፍለጋ ፣ ሀብት ፍለጋ ፣ ወደ ውጭ ለመሄድ ፍለጋ ፣ ዝና ፍለጋ ሲሆን መጨረሻው ፍቺ ይሆናል። ለምን ቢባል እዚህ ላይ ትዳርን ፍለጋ ሳይሆን፤ የአብሮነት ኑሮ ሳይሆን ፤ የመቻቻልና የመተሳሰብ ሳይሆን የጥቅምና የጥቅም ብቻ በመሆኑ የፍቺ ሊያጋጥም ይላል።
  3.  ምንም እንኳን ከራስዎ የሚስማማ ሰው ብያገኙም ነገር ግን ትዳር በራሱ ከባድ ስለ ሆነ በመክበዱም የተነሳ ፍቺ ሊፈጠር ይችላል።
  4.  ፍቺ ስያጋጥም ትዳርን ላለማፍረስ የሚደረጉ መወያየትና መፍትሄ ማስቀመጥ ላይ ደካማና በተጨማሪም አስታራቂ ሁነው በማህል ላይ የሚገቡ ሰዎች ከማስታረቅ ይልቅ ነገሩን አባብሰው በፍቺ እንድያበቁ ማድረግ የሚሉ ናቸው።

  በአጠቃላይ ከላይ የተገለጹ ችግሮች ራሳችን ምናደርጋቸው መፍትሄስ ምን ይመስላሉ የሚሉትን እናያለን፤

  • በመሀከላችን ግጭት ስያጋጥመን ግጭቱን ስሜታዊ በለሆን ሚዛናዊ ማድረግ
  • የማያስማሙ ነገሮች ሲያጋጥሙ በአንድነት ማስወገድ ወይም እንዴት ማስወገድ እንዳለብን መወሰን ፤ በግልጽና በቀጥታ መወያየትና መነጋገር፤ 
  •  በተጨማሪም በምንወያያቸው ርእሶች ያለፉ ጥፋቶች እያነሳን መወቃቀስ የለብንም። መወያየት ያለብን ስለ አሁኑ ስለተፈጠረው ጉዳይ ብቻ ነው።
  • ጥቅምን ፍለጋ ተብሎ ትዳርን አለመመስረት።
  • ከአቅማቹ በላይ  ሲሆን ደግሞ ባለሞያን ማማከር

   

  Read more »
RSS